የሀገር ውስጥ ዜና

በሀገር ላይ ጉዳት ሊያደርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት በመስራት ውጤት መመዝገቡ ተገለፀ

By Feven Bishaw

August 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ በመስራት ውጤት መመዝገቡን ገለጸ፡፡

አገልግሎቱ በበጀት ዓመቱ ወንጀል ነክ ጉዳዮችን መሠረት በማድረግ ባካሄደው ዝርዝር ፍተሻና የማጥራት 310 ከልዩ ልዩ ወንጀሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ወንጀል ነክ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ትንተና በማድረግ የህግ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ ለሚመለከታቸው አካላት ተላልፎ በሂደት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከእነዚህ ጉዳዮች መካከል ህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ የማጭበርበር ወንጀል፣ የታክስ፣ የኮንትሮባንድ ንግድ፣ የሙስና፣ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝዉዉር፣ ማስገደድና ማስፈራራት፣ ሃብት ማሸሽ፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ እና ከሌሎች ወንጀሎች ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆናቸውም ተመላክቷል።

እነዚህ የወንጀል ድርጊቶች በቢሊየን ብር የሚቆጠር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የነበሩና ያደረሱ መሆናቸው መለየቱና በወንጀል ድርጊቱም በተለያየ ደረጃ ተሳትፎ እንዳላቸው የተጠረጠሩ 2 ሺህ 273 ግለሰቦችና ሌሎች አካላት ተለይተው በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በሂደት ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ከፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-