የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጋር መከሩ

By Feven Bishaw

August 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከሱዳን የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ ጋር በፅህፈት ቤታቸው ዛሬ ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው÷ በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ በሆኑ ጉዳዮች እና በተለይም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በሱዳን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማድረግ ላይ ስለሚገኙት ጥረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለልዩ መልዕክተኛው መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በወቅቱ በሱዳን ሰላም እና ፀጥታን በዘላቂነት ለማስፈን በጋራ ለመስራት ሁለቱ ወገኖች ተስማምተዋል።