ዓለምአቀፋዊ ዜና

በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

By Meseret Awoke

June 21, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በብራዚል የኮሮና ቫይረስ 50 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች ህይወት ማለፍ ምንያት መሆኑ ተነግሯል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታትም የሟቾች ቁጥር 1 ሺህ 22 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ሃገሪቱ የመጀመሪያውን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ያረጋገጠችው በየካቲት ወር መጨረሻ ሲሆን፥ በአሁኑ ወቅት ቁጥሩ አንድ ሚሊዮን መሻገሩ ተሰምቷል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ በአለም አቀፍ ደረጃ 8 ነጥብ 75 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን፥ ከ464 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በተጨማሪም ከ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ሰዎች በላይ ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ያመለክታል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ