የሀገር ውስጥ ዜና

313 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Mikias Ayele

August 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 313 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ተመላሾቹ 263 ወንዶች፣ 44 ሴቶች እና 6 ጨቅላ ሕጻናት ሲሆኑ÷ ከእነዚህ መካከልም 24 እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡