አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በስንዴ ሰብል ለመሸፈን ከታቀደው ውስጥ እስከ አሁን ከ708 ሺህ ሔክታር በላይ መሸፈን መቻሉን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በ2016/17 የመኸር ምርት ዘመን ከ1 ሚሊየን ሔክታር በላይ በስንዴ ሰብል በመሸፈን 43 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የስንዴ ምርታማነትን በሔክታር ከነበረው 34 ነጥብ 3 ወደ 41 ነጥብ 2 ኩንታል ለማሳደግ እየተሠራ ነው መባሉን የቢሮው መረጃ አመላክቷል፡፡
ዕቅዱን ለማሳካትም በፊት ከነበረው በተለየ መንገድ ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ ተሰራጭቷል ተብሏል፡፡