የሀገር ውስጥ ዜና

ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታና ኩራት አመጣህለት – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

By Mikias Ayele

August 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታና ኩራት አመጣህለት ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንቷ ኢትዮጵያ በፓሪሱ ኦሎምፒክ በአትሌት ታምራት ቶላ  የመጀመሪያውን ወርቅ በማግኘቷ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም አትሌት ታምራት ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታና ኩራት አመጣህለት፣የዛሬው ድል ልዩ ትርጉም አለው ብለዋል፡፡