የሀገር ውስጥ ዜና

በሐረማያ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅና አካባቢዎቻቸው የተቋረጠው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገልግሎት ተመለሰ

By ዮሐንስ ደርበው

August 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረማያ፣ ሐረር፣ ጅግጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት መመለሱ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚያሥተዳድረው ባለ 132 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ዛሬ 5 ሠዓት ከ30 ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት ኃይል ተቋርጧል መባሉን መዘገባችን ይታወቃል፡፡

ብልሽቱን ተከትሎም በተደረገው ርብርብ የጥገና ሥራው ተጠናቅቆ ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡