አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 100 ቀናት ለ216 ሺህ 328 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
ምርመራው ከመጋቢት 4 ቀን እስከ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የተካሄደ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም 32 ሚሊየን ሰዎች በቤት ለቤት ዳሰሳ መታየተቻውንም አስታውቋል።
በእነዚህ ቀናቶች በተደረገ ምርመራም 4 ሺህ 532 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ነው ያለው።
በተጨማሪም ንክኪ ያላቸው 31 ሺህ 573 ሰዎች ተለይተው 708 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸውም ገልጿል።
እንዲሁም ከጥር 15 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለ764 ሺህ 948 ተጓዞች ልየታ እና ክትትል ተደርጓልም ነው የተባለው።
13 ሺህ 859 የመታከሚያ አልጋዎች የተዘጋጁ ሲሆን 4 ሺህ 500 የጤና ባለሙያዎች ተቀጥረው 12 ሺህ በጎ ፈቃደኞች መሰማራታቸውም ተጠቅሷል።
ቫይረሱን ለመከላከልም 513 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የግል መከላከያ ቁሳቁሶች በሃገሪቱ ተሰራጭተዋል።