የሀገር ውስጥ ዜና

የመስኖ ስታንዳርድና ደንብ መስኖን እንደ ተቋምና ዘርፍ ማሳደግ ያስችላል- አብርሃም በላይ (ዶ/ር)

By Melaku Gedif

August 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር የመስኖ ስታንዳርድ እና ደንብ ዶክመንት ዝግጅት የሥራ ሒደት ተገምግሟል፡፡

የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የመስኖና ቆላማ አካባቢ የመስኖ ስታንዳርድ እና ደንብ መስኖን እንደ ተቋምና ዘርፍ ማሳደግ ያስችላል፡፡

ስለሆነም የመስኖ ስታንዳርድ እና ደንብ በልዩ ትኩረት እና ጥራት ሊሰራ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት፡፡

የመስኖ ስታንዳርድና ደንብ በዲዛይንና ጥናት፣ በግንባታና በመስኖ የመሰረተ-ልማት አገልግሎት አሰጣጥ ያለውን ችግር በመቅረፍ ጥራት ያለው የመስኖ አሰራሮችን በመተግበር ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ያለመ ነው ተብሏል፡፡