የሀገር ውስጥ ዜና

በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

August 16, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

የመሬት መንሸራተት አደጋው የተከሰተው ላለፉት ሦስት ቀናት በጣለው ዝናብ ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡