የሀገር ውስጥ ዜና

በአሶሳና አካባቢዋ የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው

By ዮሐንስ ደርበው

August 19, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከትናንት ጀምሮ በአሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ፣ ቶንጎ፣ መንጌ፣ ሆሞሻ፣ ኩምሩክ እና አካባቢዎቻቸው የተቋረጠውን የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ወደ አገልግሎት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ከመንዲ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ አሶሳ ከተማ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ እያጋጠመው ባለው ተደጋጋሚ ብልሽት ምክንያት ኃይል መቋረጡ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም እየተከናወነ ያለው የጥገና ሥራ እስከሚጠናቀቅ በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትግዕስት እንዲጠብቁ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ጥሪ አቅርቧል፡፡