የሀገር ውስጥ ዜና

ለውጭ ሀገራት ከሚቀርብ የኃይል ሽያጭ 300 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት አቅጃለሁ – ተቋሙ

By ዮሐንስ ደርበው

August 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የበጀት ዓመት ለውጭ ሀገራት የሚቀርበውን ኃይል ሽያጭ ተደራሽነት በማስፋት 300 ሚሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 20 ሺህ 522 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ከውኃ፣ ከንፋስና ከደረቅ ቆሻሻ ማመንጨት መቻሉን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሸብር ባልቻ (ኢ/ር) ገልጸዋል፡፡

ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ከቀረበው ኃይልም 20 ቢሊየን ብር ገቢ መገኘቱን ጠቅሰው÷ ከዚህም ውስጥ ለውጭ ገበያ ከቀረበ የኃይል ሽያጭ 140 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል፡፡

ግንባታቸው እየተከናወነ የሚገኘው አምስት ትልልቅ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ ከዘርፉ የሚገኘው ተጠቃሚነት እንደሚያድም አመላክተዋል፡፡