የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት ይገባል- ከንቲባ አዳነች

By Melaku Gedif

August 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በገበያ መር፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ የበቃና የሰለጠነ የሰው ሃይል የማፍራት ጉዳይ ወሳኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠኗቸውን ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷የሀገርን እድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥ በገበያ መር፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ የበቃና የሰለጠነ የሰው ሃይል የማፍራት ጉዳይ ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የቴክኖሎጂ አቅም የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት በመሆኑ በዚህ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዛሬዎቹ ተመራቂዎች የዚሁ ጥረት ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው÷ ለከተማዋ ልማትና እድገት የላቀ ሚናቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

ተመራቂዎች በ22 የተለያዩ ዘርፎች የሰለጡኑ ሲሆን÷30 በመቶ የንድፈ-ሃሳብ 70 በመቶ ደግሞ የተግባር ሥልጠና የወሰዱ መሆቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡