የሀገር ውስጥ ዜና

ለሀገራዊ የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ መሆኑ ተመላከተ

By ዮሐንስ ደርበው

August 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሀገራችን የዕድገት ጉዞ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ፡፡

የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ዛሬ 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄዱን አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

በስብሰባውም የምክር ቤቱን አጠቃላይ የስራ ክንውን፣ የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸምን ገምግመናል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የአይ ቲ ፓርክን በተመለከተ በተሰጡ ስራዎች ላይ የክንውን ሪፖርት መገምግማቸውን ጠቅሰው÷ የብሔራዊ ዲጂታል የመንግስት ስትራቴጂ ቀርቦ በምክር ቤቱ አባላት ውይይት እንደተደረገበት አመላክተዋል፡፡