የሀገር ውስጥ ዜና

በማሻሻያ ሥራ ምክንያት ነገ በአዲስ አበባ የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል ይቋረጣል

By ዮሐንስ ደርበው

August 22, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ማሻሻያ ስራ ለማከናወን ሲባል ነገ በአዲስ አበባ ከተማ የተወሰኑ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደሚቋረጥ ተገለጸ፡፡

በዚህም ከጠዋቱ 3 ሠዓት ከ30 እስከ 11 ሠዓት ድረስ በቦሌ ጎሮ አካባቢ፣ በሰፈራ፣ ከረሜላ ፋብሪካ፣ ታቦት ማደሪያ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል ተብሏል፡፡

በተጠቀሱት አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞችም ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል፡፡