የሀገር ውስጥ ዜና

በጋምቤላ ክልል አዲሶቹን አመራሮች የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

August 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል አዲሶቹን አመራሮች የሚደግፍ ሰልፍ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ነው።

የድጋፍ ሰልፉ በክልሉ ርዕሰ ከተማ ጋምቤላ፣ በአቦቦ፣ በኢታንግ ልዩ ወረዳ እና በሌሎች አካባቢዎች ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

የድጋፍ ሰልፉ ተሳታፊዎች ከለውጡ አመራር ጎን በመቆም ልማትን እናረጋግጣለን፣ በመተባበርና አንድ በመሆን የማንፈታው ችግር የለምና የተገኘውን ሰላም እንጠብቃለን የሚሉ መልዕክቶችን እያሰሙ እንደሚገኙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡