የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

August 24, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ዱርሲቱ ቢሊሱማ ቀበሌ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካሳዬ አበበ እንደገለፁት÷ አደጋው የተከሰተው ከአዲስ አበባ ወደ ጅቡቲ ይጓዝ የነበረ የነዳጅ ቦቴ ከባድ መኪና ከባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ  ጋር በመጋጨታቸው ነው፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ