አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የስዊችጊር ቅየራ ሥራን በራስ አቅም በማከናወን ከ2 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ማዳን መቻሉን አስታውቋል፡፡
በዘርፉ በ2016 በጀት ዓመት በ22 ማከፋፈያ ጣቢያዎች የ15 እና የ33 ኪሎ ቮልት ስዊችጊር ቅየራ ሥራ በራስ አቅም ማከናወን መቻሉ ተገልጿል፡፡
በጣቢያዎቹ የስዊችጊር ቅየራ ለማከናወን 2 ሚሊየን 463 ሺህ ዶላር ግምታዊ ሥራ ለመሥራት ታቅዶ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
በተከናወነው ሥራም 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ወጪ ማዳን መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም የ11 ማከፋፈያ ጣቢያዎች የሥዊች ጊር ቅየራ ሥራ በሒደት ላይ እንደሚገኝ የተቋሙ መረጃ ያመላክታል፡፡