የሀገር ውስጥ ዜና

የግብርና ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በዱብቲ ወረዳ አረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

By Melaku Gedif

August 30, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች እና ሰራተኞች በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴን (ዶ/ር) ጨምሮ ሚኒስትር ዴዔታዎች፣ ዳይሬክተሮች እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

በም/ርዕሰመስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስትባባሪ አቶ አሊ መሃመድ እና ሌሎች የክልሉ ግብርና ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች መሳተፋቸውንም የአፋር ክልል መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡