አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር፣ ሶማሌ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደቱን እስከ ጥቅምት አጋማሽ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ኮሚሽኑ አስታወቀ፡፡
እየተሠሩ ያሉ እና በቀጣይ የታቀዱ ተግባራትን በተመለከተ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ከግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራዎች እየተከነባወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
በሲዳማ ክልል እየተካሄደ ያለው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትም ነገ ተጠናቆ የተደራጀው አጀንዳ ለኮሚሽኑ እንደሚላክ አመላክተዋል፡፡
በትግራይ እና አማራ ክልሎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደትን ለማከናወን ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠው÷ ሁኔታዎች ሲመቻቹ ተግባራቱ እንደሚከናወኑ አመላክተዋል፡፡
በፍቅርተ ከበደ፣ ጀማል ከዲሮ እና ታመነ አረጋ