አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ “እንሥራ” የሸክላ ስራ ማዕከልን በዛሬው እለት ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በተጨማሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉብኝቱን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ “እንሥራ በተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከል ለምትሠሩት እህቶቼ እና እናቶች እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ” ብለዋል።
“የድካማችሁን ፍሬ በማየቴ ደስ ብሎኛል” ሲሉም ገልፀዋል።
“እንሥራ” የተሰኘው አዲስ የሸክላ ሥራ ማዕከል ግንባታው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ባሳለፍነው ቅዳሜ መመረቁ ይታወሳል።
በማዕከሉ 1 ሺህ በሸክላ ስራ ላይ የተሰማሩ እናቶች የመስሪያና የመሸጫ ቦታዎች ከተሟላ የማምረቻ ቦታ እና ከተሟላ ቁሳቁሶች ጋር የሚያገኙበትም ነው።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።