የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባዔ እየተሳተፈች ነው

By ዮሐንስ ደርበው

September 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ ልዑክ በ9ኛው የቻይና-አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባዔ እየተሳተፈ ነው።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መጪው ጊዜ በጋራ መሥራትን የሚፈልግ በመሆኑ ቻይና ከአፍሪካ ጋር የተሻለ አጋርነትን ትፈልጋለች ብለዋል።

የደቡብ-ደቡብ ግንኙነቶችን ለማጠናከር ብሎም ወደ ጋራ ልማትና ብልፅግና ለመሸጋገርም ቻይና እንደምትሠራ አረጋግጠዋል፡፡

አሁን በጋራ አዲስ ታሪክ እንድንፅፍ መተባበር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በጉባዔው ላይ የቻይና-አፍሪካን ግንኙነት እና ትስስር በይበልጥ የሚያሳድጉ ጉዳዮች እንደሚነሱ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ነገ በሚጀመረው የቻይና-አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የበርካታ ሀገራት መሪዎች ቤጂንግ እየገቡ ነው፡፡

ከጉባዔው ጎን ለጎን ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ወዳጅነቷን ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ እንደምትሠራ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ