የሀገር ውስጥ ዜና

በመሪዎች ደረጃ የአማራ እና አፋር ክልሎች የሰላም መድረክ እየተካሄደ ነው

By Tibebu Kebede

June 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመሪዎች ደረጃ የአማራ እና አፋር ክልሎች የሰላም መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

በሰላም መድረኩ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመሥገን ጥሩነህ እና የአፋር ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ አወል አርባ ተገኝተዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የየክልሎቹ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊዎችም ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

መድረኩ የአጎራባች ወረዳዎች ባላቸው ሁሉን አቀፍ መስተጋብር አልፎ አልፎ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታትና መልካም ተሞክሮዎችን ለማስፋት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ከሰላም መድረኩ ቀደም ብሎ ርዕሰ መስተዳድሮቹ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ምክንያት በማድረግ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡

ሁለቱ ክልሎች ከ400 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ባለው አራት ዞኖች እንደሚዋሰኑ አብመድ ዘግቧል።