የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች የአረንጓዴ ዐሻራ ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጥሪ አቀረቡ

By Feven Bishaw

June 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፊልም፣ በግራፊክ ሥነ ጥበብ፣ በፎቶግራፍ፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በካርቱን ሥዕል እንዲሁም በልዩ ልዩ ዘርፎች የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች አነቃቂ የአረንጓዴ ዐሻራ ቪዲዮዎችን ቪዲዮዎችን አዘጋጅተው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን እንዲያጋሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌግራም ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የዚህ ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከተጀመረ ሁለት ወር ሊሞላው መሆኑን አንስተዋል፡፡