የሀገር ውስጥ ዜና

ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

By ዮሐንስ ደርበው

September 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደኅንነት ጋር በመሆን በሕገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገባ ዕቃ መያዙን ነው ያስታወቀው፡፡

ዕቃዎቹን ወደ አዲስ አበባ በማስገባት ሊያሰራጩ ሲሞክሩ ገላን ኮንዶሚንየም አካባቢ ሹፌሩንና ረዳቱን ጨምሮ የኮንትሮባንዱ ዕቃዎቹ መያዛቸውን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡