የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ልዩነታቸውን በውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለጸ

By Feven Bishaw

June 26, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ የአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ገልጸዋል።

ሙሳ ፋኪ ማህመት ከኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተወያይተዋል።