አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጀሞ 2 እስከ ጀኔራል ዊንጌት የሚገነባው የፈጣን አውቶብስ መንገድ ተጀመረ።
የመንገዱን ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አስጀምረውታል።
መንገዱ በአጠቃላይ 20 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን ወደ ሁለት አቅጣጫ የሚዘረጋ ነው ተብሏል።
የፈጣን አውቶብስ መንገዱ አዲስ ከተማ፣ ልደታ፣ ቂርቆስና ኮልፌ በመሳሰሉ ቦታዎች የአውቶብስ መቆሚያዎች ይኖሩታልም ነው የተባለው።
በቀጣይም ከ20 በላይ የአውቶብስ የፍጥነት መንገድ መንገድ ፕሮጀክቶች መታቀዳቸውን ኢንጂነር ታከለ ኡማ ተናግረዋል።
አያይዘውም የከተማ አስተዳደሩ የትራንስፖርት ችግርን ለመፍታት የብዙሀን ትራንስፖርትን ማዘመንና ማሳደግ ላይ ያተኩራልም ነው ያሉት።
ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜና በተቀመጠላቸው የጥራት ደረጃ እንደሚጠናቀቁ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የአውቶብስ የፍጥነት መንገድ ፕሮጀክቱን የፈረንሳይ ኩባንያ የሚያከናውነው ይሆናል።