የሀገር ውስጥ ዜና

የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ ትራንስፎርመር በክሬን የጫኑ ግለሰቦችን እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

June 27, 2020

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የመብራት ኃይል ሠራተኞች ነን በሚል ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል አስተላላፊ የሆነ ትራንስፎርመር በክሬን ጭነው ለማምለጥ የሞከሩግለሰቦችን እሰከጫኑበት ክሬን እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቦሌ ክክፍለ ከተማ ከተማ ወረዳ 10 ሐያት ቁጥር 1 በሚባል አካባቢ በትናንትናው እለት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 አካባቢ ለ80 አባወራዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘውን ትራንስፎርመር ከመስሪያ ቤቱ ዕውቅና ውጭ በክሬን ተሸከርካሪ ታግዘው በመስረቅ ለማምለጥ ሲመክሩ በአካባቢው ነዋሪ ጥርጣሬ ለፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ እጅ ከፍንጅ ሊያዙ መቻላቸውን የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኮማንደር ያሲን ሁሴን ገልዋል።