አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአሚሰም የተልዕኮ አፈፃፀም ወሳኝ የሆኑ ግብአቶች ሶማሊያ ባይደዋ አድርሶ ለተመለሱ የቅልፈት ጉዞ አባላት በዶሎ አዶ ከተማ የጀግና አቀባበል ተደረገ፡፡
በአቀባበል ስነ-ሰርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ ንግግር አድርገዋል፡፡
ዋና አዛዡ በንግግራቸው ጠላት የቅልፈት ጉዞውን ለማደናቀፍ በረቀቁ ፈንጂዎች ደፈጣና የተለያዩ የጥቃት ሙከራዎች እንቅፋት ለመፍጠር ቢሞክርም ሰራዊቱ በጥምረት እቅዱን ለማክሸፍ ከግብ ማድረስ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
ዋና አዛዡ የተሠራው ታሪካዊ ስራ የተቋማችንን የማድረግ አቅም አጉልቶ የሚያሳይ ለወዳጅ ኩራት የሀገራችን ክፋ ለሚያስቡ ደግሞ ትምህርት የሰጠ መሆኑን ጠቁመው በግዳጅ ለተሳተፉ አካላት ሁሉ ምሥጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የቅልፈት አስተባባሪና የሁለተኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል በስፋት ፋንቴ ስለ ቅልፈቱ እቅድ የተግባር ክንውን ያጋጠሙ ችግሮችና ሠራዊቱ ስለወሰዳቸው አኩሪ መፍትሄዎች ኦንዲሁም የተገኘው ስኬት ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ታሪካዊ ሀላፈነታቸው የተወጡ አባላት በሊበን ዞን የዶሎ ወረዳ ህዝብ በነቂስ ወጥተው የተቀበሉ ሲሆን ለአባላቱም የ200 የእርድ ፍየሎች ስጦታ ማበርከታቸውምን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡