የሀገር ውስጥ ዜና

መሳላ ትውፊቱን ጠብቆ እንዲቀጥል ወጣቱ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

By ዮሐንስ ደርበው

September 24, 2024

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የከምባታ የዘመን መለወጫ መሳላ በዓል ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል ወጣቱ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ የዱራሜ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡

የመሳላ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዱራሜ ከተማ በርካታ ወጣቶች የተሳተፉበት ሁለት ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍን የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሂዷል፡፡

በዚሁ ወቅት የዱራሜ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እሸቱ አደሮ÷ የከምባታ የዘመን መለወጫ መሳላ በዓል ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል ወጣቱ ሚናውን እንዲወጣና የባህል መበረዝን እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።

ወጣቶች በበኩላቸው÷ የበዓሉን ዕሴት ለትውልድ ለማስተላለፍ ወጣቱ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አንድነቱን አጠናክሮ ለልማት ማዋል ይገባል ብለዋል፡፡

የሩጫው አዘጋጅ ቪዚት ከንባታ አስጎብኝና ኤቨንት ሥራ አስኪያጅ ሳምሳሶን ቶማስ÷ የሩጫው ዓላማ የመሳላ በዓልን ለወጣቱ በወጉ ማስተዋወቅ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በጥላሁን ይልማ፣ ጀማል ከዲሮ እና ኢዛናዊት በኩረፅዮን