አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ እና ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት የንግድ እና የልማት ባንክ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል የሚውሉ ግብአቶችን ዛሬ ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ።
የተደረገው ድጋፉ 100 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 160 ሺህ የሚሆኑ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስከኮች ናቸው።
ባንኩን ወክለው የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ በድጋፍ የተገኙት ማስኮች በሃገር ውስጥ በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ የተመረቱ መሆናቸውን ተናግረዋል ።
ይህም የኢንዱስትሪ ልማቶችን የሚያበረታታ እንደሆነም ገልፀዋል።
መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ባለፈም የልማት ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ ወሳኝ እንደሆንም አቶ አህመድ ሺዴ ጠቁመዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ብለዋል።
የተለያዩ አጋር ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ የኮሮና ቫረስን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።
ዛሬ ድጋፍ ላደረው የንግድ እና የልማት ባንክም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
በቅድስት ብርሃኑ