የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ ተካሄደ

By Melaku Gedif

November 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 1፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ሕዝባዊ የስፖርት እንቅስቃሴ (ማስ ስፖርት) ተካሂዷል ፡፡

መርሐ ግብሩ”የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

የስፖርት እንቅስቃሴው በየካ ፣ ቦሌ፣ ቂርቆስ፣ ልደታ፣ ላፍቶ እና ሌሎች ክፍለ ከተሞች መካሄዱን የከተማዋ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡