የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተሾመ ሹንዴ ከተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ጋር መከሩ

By Meseret Awoke

November 21, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተሾመ ሹንዴ በቅርቡ ከተመረጡት ከሶማሊላንድ አዲሱ ፕሬዚዳንት አብዱልራህማን ሞሃመድ አብዱላህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸውን የዘገበው ሃንጉል ፕረስ ነው፡፡

አምባሳደር ተሾመ ከኢትዮጵያ መንግስት የተላከ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አዲስ ለተመረጡት ፕሬዚዳንት አድርሰዋል፡፡