የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ 24 ሰዓታት 356 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

July 18, 2020

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 886 የላብራቶሪ ምርመራ 356 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 503 መድረሱንም ሚኒስቴሩ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል።