የሀገር ውስጥ ዜና

ታጥቀው ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ

By ዮሐንስ ደርበው

November 27, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ በአንካሻ ገብርኤል ቀበሌ ታጥቀው ጫካ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ኃይሎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀበሉ፡፡

በቀጣናው በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚመራው ኮማንድ ፖስት ባደረገው የተቀናጀ ሥራ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 22 ግለሰቦች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ሙሉ ትጥቃቸውን አስረክበዋል፡፡

ታጣቂዎቹ የመንግሥትን ሰላም ጥሪ መቀበላቸውም ማኅበረሰቡ ግብርናን ጨምሮ መደበኛ ሥራውን እንዲያከናውን ያስችላል መባሉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህ ሣምንት በወረዳው በዚሁ ቀበሌና በቡርጅ ቀበሌዎች ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 34 ግለሰቦች እጅ መስጠታቸውም ተገልጿል፡፡