የሀገር ውስጥ ዜና

መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው

By ዮሐንስ ደርበው

December 01, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ወደ ማሠልጠኛ ማዕከል ሽኝት ተደረገላቸው፡፡

ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶች በከተማዋ ከሚገኙ አራት ክፍለ ከተሞች የተመለመሉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በአባልነት በመቀላቀላቸው ኩራት እንደተሰማቸው መግለጻቸውን የደብረ ማርቆስ ከተማ ኮሙኒኬሸን ጽሕፈት መረጃ አመላክቷል፡፡