የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ታዬ ከሜሪ ጆይ የስራ ሃላፊዎች  ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

December 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ  ከሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ፣ከየሜሪ ጆይ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ይስማሽዋ ስዩም እና ከቦርድ አባላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

 

በውይይታቸው  ሜሪ ጆይ በህፃናት፣ አረጋዊያን እና ሴቶች በትምህርት፣ በጤና እና በተለያዩ የስራ መስኮች ላይ በሰራው  መልካም ተግባሮች ላይ መምከራቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡