የሀገር ውስጥ ዜና

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት በጋምቤላ ከተማ የቱሪስት መስህቦችን ጎበኙ

By yeshambel Mihert

December 05, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን ጎብኝተዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ከጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ጋር በመሆን ነው በከተማው የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን የጎበኙት፡፡

በጉብኝታቸውም የጋምቤላ ከተማን ለሁለት ከፍሎ የሚያልፈውን ታሪካዊው የባሮ ድልድይን እና ዓመቱን ሙሉ የሚፈሰውን የባሮ ወንዝን መመልከታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡