የሀገር ውስጥ ዜና

5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍቲኔት የሚተገበርባቸው 31 ወረዳዎች ተሽከርካሪ ተበረከተላቸው

By ዮሐንስ ደርበው

December 06, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል የእርሻ ልማት ቢሮ በክልሉ 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ለሚተገበርባቸው 31 ወረዳዎች 31 ተሽከርካሪዎችን አስረከበ፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በ5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ለሚከናወኑ ሥራዎች የሚያገለግሉ ናቸው መባሉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡

ፕሮግራሙን በውጤታማነት ለመተግበር በሚደረገው ጥረትም በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ተገልጿል፡