የሀገር ውስጥ ዜና

የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው- አገልግሎቱ

By yeshambel Mihert

December 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት ምክንያት በተፈጠረ ችግር በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ እንዳጋጠመ አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስም በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ የጠየቀው አገልግሎቱ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት እንደሚያሳውቅም ገልጿል፡፡