የሀገር ውስጥ ዜና

በብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዋዜማ በጋሞ ባህልና ምርምር ማዕከል የእራት መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው

By yeshambel Mihert

December 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዋዜማ በአርባምንጭ ከተማ ጋሞ ባህልና ምርምር ማዕከል የእራት ምሽት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች ፣የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም የጋሞ አባቶችና የሁሉም ብሔሮች ብሔረሰቦች የባህል ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛል።