የሀገር ውስጥ ዜና

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት

By Feven Bishaw

December 07, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ እየተከበረ ለሚገኘው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል መሳካት በሚዲያው ዘርፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ  የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበረከተለት።

 

“ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሃሳብ  የዘንድሮው የብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል በነገው ዕለት በደማቅ ስነ-ስርዓት ፍፃሜውን ያገኛል።