አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በአርባ ምንጭ ከተማ በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስታወቀ፡፡
የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን በሰጡት መግለጫ÷19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ከሕዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር መቆየቱን አንስተዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የበዓሉ ማጠቃለያ መርሐ ግብር በስኬት ተከብሮ መጠናቀቁን ገልፀዋል።
በዓሉ በስኬት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የአርባምንጭ ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች እንዲሁም የጸጥታ አካላት ላበረከቱት አስተዋፅኦም ምስጋና አቅርበዋል፡፡