የሀገር ውስጥ ዜና

የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት ስልጠና ያጠናቀቁ ወጣቶች ተመረቁ

By ዮሐንስ ደርበው

December 08, 2024

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማኅበረሰብ አገልግሎት 11ኛ ዙር ሰልጣኞች ተመረቁ፡፡

ወጣቶቹ 1 ሺህ 444 ሲሆኑ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሥልጠናቸውን መከታተላቸው ተገልጿል፡፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አሥተዳደሮች የተወጣጡ መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡

ተመራቂ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ በሁሉም ክልሎች ተሰማርተው በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር ግንባታው ገንቢ ሚናቸውን እንደሚወጡ መገለጹን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡