የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ንግድ ድርድር ዝግጅት በጄኔቫ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

December 10, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልዑካን ቡድን በጄኔቫ የዓለም ንግድ ድርድር ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

በቅርቡ ኢትዮጵያ የምታካሂደው 5ኛው የስራ ቡድን ስብሰባን ስኬታማ ለማድረግ ከአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ኒውዚላንድ እና አውሮፓ ህብረት የንግድ ተደራዳሪዎች ጋር ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል፡፡

ይህን መሰል ውይይቶች ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የምታደርገውን ድርድር ያቀላጥፋል ተብሎ እንደሚታመን ከጉምሩክ ኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡