የሀገር ውስጥ ዜና

ዓለም አቀፉ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ ፕሬዚዳንት ታዬ በተገኙበት እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

December 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በተገኙበት 21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የማጠቃለያ መድረክ በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የምክር ቤት አባላት፣ የፌደራል የሥነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)፣ ሚኒስትሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

21ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን “ወጣቶችን ያማከለ የፀረ-ሙስና ትግል የነገን ስብዕና ይገነባል” በሚል መሪ ሃሳብ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል።

በመድረኩ ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን በ2016 ዓ.ም ሙስናን በመታገል ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጥቶታል፡፡