ስፓርት

መቻል እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

December 11, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ11ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን አቻ ተለያዩ፡፡

10 ሠዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ማስቆጠር ባለመቻላቸው ያለምንም ግብ ጨዋታቸውን በአቻ ውጤት አጠናቀዋል፡፡

እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ስሑል ሽረ መቐለ 70 እንደርታን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ÷ ጎሉን ብርሃኑ አዳሙ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡