የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስነ-ህዝብ ምክር ቤት የምክክር ጉባዔ እየተካሄደ ነዉ

By Feven Bishaw

December 12, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ያዘጋጀው ክልላዊ የስነ-ህዝብ ምክር ቤት የምክክር ጉባዔ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነዉ።

“የተመጠነ ቤተሰብ ለደስተኛ ኑሮና ለፍትሃዊ ተጠቀሚነት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው ጉባዔ የክልሉን ስነ-ህዝብ በሚመለከት ጥናታዊ የዳሰሳ ጽሑፍ እንዲሁም የስነ-ህዝብ የሰባት ዓመት ፕሮግራም ዕቅድ ሰነዶች ቀርበዉ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉባዔው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው እና ሌሎች የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የምክር ቤቱ አባላትና ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡