የሀገር ውስጥ ዜና

በምዕራብ ወለጋ ዞን የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው

By Feven Bishaw

December 13, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው።

በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦነግ ታጣቂዎች ለቀረበው የሰላም ጥሪ ምላሽ በመስጠት ወደ ካምፕ በመግባት ላይ እንደሆኑ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

በኦሮሚያ ክልል መንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንን ተከትሎ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ መግባት መጀመራቸው ይታወቃል።