ስፓርት

አትሌት ንብረት መላክ የባንግሴን ግማሽ ማራቶን ውድድርን አሸነፈ

By amele Demisew

December 15, 2024

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ንብረት መላክ በታይላንድ ቾን ቡሪ የተካሄደውን የባንግሴን ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸንፏል፡፡

አትሌት ንብረት ርቀቱን 1 ሰዓት 2 ደቂቃ ከ32 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ መሆን የቻለው፡፡